ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ ኑሮዋን በውጭ ሀገር ያደረገችው ታዳጊ ሊያ ካሳ በባህርዳር ከተማ ለሚገኘው ምስራቅ ግዮን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 25 ኮምፒውተር፣ 2 ድጅታል ማይክሮስኮፕ፣ ለ200 ተማሪዎች የሚሆን የመማሪያ ቁሳቁስ እና በትምህርት ቤቱ የክረምት ትምህርት ለሚማሩ ለ100 ተማሪዎች የ1ወር ምገባ ፕሮግራም ወጭ ድጋፍ አድርጋች ።
በጎ ፈቀዳኛዋ ሊያ በትምህርት ቤቱ ከፖርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ጋር በመተባባር ከኃይሌ ማናስ አካዳሚ፣ ከባህር ዳር ስቲም ሴንተር እና በውጭ ሀገር የሚማሩ ተማሪዎች የሚያስተምሩበት የክረምት ትምህርት ተጀምሯል።
በጎፈቃደኛዋ ታዳጊ ሊያ ካሳ ሁሉም ህጻናት ጥሩ የትምህርት እድል እንዲያገኙ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማሰብ ድጋፍ ማድረጓን ገልጻለች። በቀጣይም የትውልድ ሀገሬ ህጻናትን የማገዝ ህልም አለኝ ያለችው ታዳጊ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጻለች።
በድጋፍ ርክክቡ እና የትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የባህር ዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሙሉዓለም አቤ /ዶክተር/ በጎፈቃደኛዋ ሊያ ካሳ ላደረገችው ድጋፍ አመሰግነዋል። የዚህ ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለዬ ሁኔታ ትምህርት ላይ ትኩረት አድርጎ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የፖርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ የአማራ ክልል አስተባባሪ አቶ አብዮት አሸናፊ ድርጅቱ በክልሉ 34 ትምህርት ቤቶችን ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር መገንባቱን ገልጸው አሁን ደግሞ የክረምት የትምህርት በጎፈቃድ አገልግሎት ስራ እያስተባበረ መሆኑን ገልጸዋል። ድርጅቱ እንደ ሊያ አይነት በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የክረምት የትምህርት በጎፈቃድ አገልግሎትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse 
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *