የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራን እና የትምህርት ተቋማት አመራሮችን የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳትን በተመለከተ ለዞን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠና መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራን እና የትምህርት አመራሮች የሙያ ፈቃድ እድሳት ዳይሬክተር አቶ ካሴ አባተ የሙያ ፈቃድና እድሳት መምህራንና የትምህርት አመራሮች ራሳቸውን እንዲያበቁና አቅማቸውን እንዲያሻሽሉ ያደረገና በሂደቱም የተማሪዎችን ውጤት እንዲሻሻል ምክንያት የነበረ ነው ብለዋል፡፡
የሙያ ፈቃድና እድሳት ለዘርፍ ምሁራን እና ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ያለው አበርክቶ የጎላ በመሆኑ ፕሮግራሙን ለማስጀመር ልዩ ትኩርት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን አብራርቷል።
በስልጠናው የሙያ ፈቃድና እድሳት መመሪያ ፣ 5ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ፣ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጀውን የሙያ ፈቃድ እድሳት እና በመመሪያዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል ።
የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የመምህራን እና የትምህርት አመራሮች የሙያ ፈቃድ እድሳት ቡድን መሪ ወ/ሮ አልማዝ ጌታቸው እና የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ የመምህራን እና የትምህርት አመራሮች የሙያ ፈቃድ እድሳት ቡድን መሪ አቶ ይልማ ጥላሁን እንደገጹት የሙያ ፈቃድ እድሳት እንደገና መጀመሩ የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ እየተመዘኑ መሄዳቸው ሀገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋቸው አብራርተዋል።
የሙያ ፈቃድ እድሳት የሚወስዱ መምህራን አንባቢም ስለሚያደርጋቸው በሙያቸው የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንደሚያስችል አስረድተዋል።
ዘገባው ኮምቦልቻ ኮሙኒኬሽን ነው
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *