በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ፡፡
——————————————–
በአሸባሪ ቡድኑ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ መገንባት በሚቻልበት ዙሪያ ከወረዳ፣ ዞንና የትምህርት ቤት አመራሮችና ከወላጆች ጋር በባሕርዳር ከተማ ምክክር ተካሂዷል ።
በመድረኩም አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች ካደረሰው ሰብዓዊ ጥፋት በተጨማሪ የትምህርት እና ሌሎች ሕዝብ የሚገለገልባቸውን ማኅበራዊ ተቋማት በማውደም የሕዝብ ጠልነቱን ማሳዬቱ ተገልጿል፡፡
የአሸባሪ ቡድን በአማራ ክልል ብቻ በወረራቸው አካባቢዎች ከ4 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ዝርፊያና ውድመት አድርሷል፡፡
በዚህም ምክያት ከ1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ሕፃናትና ታዳጊዎች ከ116 ሽህ በላይ መምህራን ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል፡፡ 

እነዚህን የወደሙ የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት እና ትምህርት ለማስጀመር ከ11 ቢሊዬን ብር በላይ እንደሚያስፈልግም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ /ዶክተር/ ገልጸዋል ። ከዚህ በተጨማሪም በተማሪዎችና ወላጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ የስነ ልቦና ቀውስ በመድረሱ ይህን የስነ ልቦና ቀውስ በመጠገን ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እንደሚጠይቅም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር ) በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሰው ሲገነቡ በነበሩበት ደረጃ ሳይሆን በተሻለ ጥራት እንደሚሆን ተናግረዋል። በዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የወደሙና የተዘረፉ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እኔም የድርሻዬን እወጣለሁ !!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በቴሌግራም https://t.me/anrse



