በደብረ ማርቆስ ከተማ መንቆረር ትምህርት ቤት በ9ሚሊየን ብር ለመማሪያ ክፋል አገልግሎት እንዲውል ታስቦ የተገነባ ህንፃ ተመረቀ።
**************
የመንቆረር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ መሠናዶ ትምህርት ቤትን የመማሪያ ክፍሎችን ችግር ለመፋታት በከተማ አስተዳደሩና በአካባቢው ማህረሰብ ተሳትፎ በ9ሚሊየን ብር ባለሁለት ወለል/g+2/ 15 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ህንጻ ተመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱም የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የከተማ ነዋሪዎችና የቀድሞው የትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎች ተገኝተዋል።



