በሰው ሀብት ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው Human Capital Operation (HCO) ፕሮግራም በተመለከተ የትውውቅ እና ምክክር መድረክ ተካሄደ።
**********
ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከገንዘብ ቢሮ ጋራ በጋራ Human Capital Operation (HCO) ፕሮግራም ላይ የትውውቅ እና ምክክር መድረክ አካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ Human Capital Operation (HCO) ፕሮግራም የሰው ልጅ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚተገበር በመሆኑ የተመደበውን ሃብት የፕሮግራሙን ዓላማ መሰረት በማድረግ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በመተግበር ለታለመለት ዓላማ ብቻ በማዋል የትምህርት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ተቋማት ከደረሰባቸው ጉዳት አንጻር መልሶ ለመገንባት ከመንግስትና ማህበረሰቡ በተጨማሪ የአጋር ድርጅቶች ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለያዩ መንገዶች የሚገኙ ድጋፎች የትምህርት ቤቶችን ችግር በመቅረፍ ሞዴል ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ አቶ መኳንንት አስገንዝበዋል።
Human Capital Operation (HCO) ፕሮግራም በአማራ ክልል ሰባት ልዩ ትኩረት በሚሹ ፣ሶስት በድርቅ ለተጎዱ እና ሶስት በግጭት ለተጎዱ ወረዳዎች በአለም ባንክ ድጋፍ እንደ ሀገር ለአምስት ዓመት የሚፈፀም ፕሮግራም መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እቅድ ዝግጅት ግምገማ እና ሀብት ማፈላለግ ዳይሬክተር አቶ ዘመነ አበጀ ተናግረዋል።
ለፕሮግራሙ እንደ ሀገር 400 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተመደበ ሲሆን ፕሮግራሙ ውጤትን መሰረት ያደረገ እና የኢንቨስትመንት ፕሮግራም ፋይናንሲንግ ሲስተምን መሰረት በማድረግ የሚፈጸም መሆኑ ተመላክቷል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *