“ተሞክሮዎችን በማለዋወጥ፣ የአፈፃፀም ልዩነቶችን በማጥበብ ትምህርት ላይ የታየውን ተስፋ ሰጭ የውጤታማነት ጅምር ማስፋትና ማጥለቅ ይገባል።”
የተከበሩ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018ዓ.ም የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከወሎ ቀጠና ትምህርት አመራሮችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ለሁለት ቀናት አካሂዷል።
በግምገማ መድረኩም የትምህርት ስራዎች ያሉበት አፈፃፀም በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። የቢሮው ያለፉት ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሱፐርቪዥን ቡድን ግብረመልስና ተማሪዎችን ለማብቃት መሰራት ያለባቸው ተግባራት ሰነድ ቀርበዋል።
በውይይቱም በትምህርት ዘርፉ የተጀመሩ መነቃቃቶች ፣ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚደረጉ ጥረቶች፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የውይይት ተሳታፊዎች አንስተዋል። በትምህርት መዋቅሩ የሚደረጉ ድጋፍና ክትትል ስራዎች ውጤት እያመጡ እንደሆነ የገለፁት ደግሞ የትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ ናቸው።
በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የሰጡት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ በበጀት አመቱ ትምህርት ላይ የሚታየው አፈፃፀም ተስፋ ሰጭ ነው ብለዋል። በግምገማ መድረኩም በርካታ ተሞክሮዎች መቅረባቸውን ያነሱት ኃላፊው ተሞክሮዎችን በሁሉም አካባቢዎች ወስዶ መፈፀም የትምህርት አመራሩ ተግባር መሆን እንዳለበት ተገልፆል። ተማሪዎችን ለማብቃት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች፣ የትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ምገባ በሁሉም አካባቢዎች ለማስጀመር የሚደረጉ ጥረቶች፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች አበረታች መሆኑን አቶ ጥላሁን ገልፀዋል። በትምህርት ዘርፉ ባለን አሁናዊ አፈፃፀም የመለወጥ እድል አለን ያሉት ኃላፊው ተሞክሮዎችን በማስፋት ከቦታ ቦታ ያሉ የአፈፃፀም ክፍተቶችን በማጥበብ ውጤት ማስመዝገብ እንችላለን ብለዋል።
በቀጣይም ተማሪ ማብቃት ስራዎች፣ ከኦንላይን ፈተና ጋር በተያያዘ ያሉትን እድሎች አሟጦ መጠቀም፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በጊዜ፣ በጥራትና ፍጥነት ማጠናቀቅ፣ የትምህርት ኢኒሸቲቮችን በተሟላ ሁኔታ መፈፀም፣ በ2018ዓ.ም የሚሰራውን የመርሱ ዝውውር በጥንቃቄና ውጤታማ በሆነ አግባብ መፈፀም፣ የኮሌጅ ትምህርት ቤቶች ግንኙነትን ማጠናከር፣ የመፅሐፍት ስርጭትና አያያዝ ስራዎችን መስራትና የድጋፍና ክትትል ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባና በሌሎችም አንኳር ጉዳዮች አቶ ጥላሁን ወርቅነህ አፅንኦት ሰጥተው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau



