
አቶ ጥላሁን ወርቅነህ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
ደሴ:የካቲት 9/2018(ትምህርት ቢሮ)የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018ዓ.ም የስድስት ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በደሴ ከተማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮነን ትምህርት ዘርፍ የምናወጣው ነገር ሁሉ ኪሳራ የለውም ኢንቨስትመንት ነው ብለዋል። በዞኑም የትምህርት ፍትሐዊነትን፣ ጥራትን፣ተገቢነትን የሚያረጋግጡ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተገልጿል።
በግምገማ መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ትምህርት ላይ የሚመጣ ውድቀትም ሆነ ስኬት በክልላችን የልማት ሴክተሮች ላይ አወንታዊም ሆነ አለታዊ ተፅዕኖ አለው ብለዋል።
ያልተማረ ትውልድ ነገን በብሩህ እይታ አለማየቱ ብቻ ሳይሆን ዛሬን ለማስቀጠል ይቸገራል ብለዋል። አለም በከፍተኛ ውድድር ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት ዋናው የመወዳደሪያ ቁልፍ ትምህርት ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግስትም ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋ ለመፍጠር ከፌደራል ስርዓቱ ጋር ተናባቢ የሆነ የ25 አመት የትምህርት ሴክተር ፍኖተ ካርታና የ5 አመት ስትራቴጅክ እቅድ እንዲሁም የ2018 በጀት አመት የትምህርት እቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ መገባቱን አንስተዋል።
የክልሉ መንግስት የትምህርት ሴክተሩን ለማጠናከር በሚያደርገው ጥረት 500 ሚሊየን ብር ተመድቦ የትምህርት ቤቶች የተማሪ ምገባ መጀመሩን አውስተዋል።
በክልሉ በአይነታቸው ሌዩ የሆኑ 3 አዳሪ ት/ቤቶችና 4 ሞዴሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶም ግንባታቸው እየተፋጠነ ነው ያሉት ኃላፊው ትምህርት ቤቶችን በ2019 ትምህርት ዘመን ስራ ለማስጀመር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በ2018 በጀት አመት በሁለም መደበኛ ተግባራት የተማሪ ተሳትፎን ጨምሮ ካለፉት 2 አመታት በእጅጉ የተሻለና ተስፋ ሰጭ እንደሆነ የገለፁት ኃላፊው በክልላችን ውስጥ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት አሁንም ድረስ ወደ ትምህርት ቤት ያልመጡ በርካታ ተማሪዎች እንዳሉ ጠቅሰዋል።
ወደ ትምህርት ቤት የመጡ ተማሪዎችን የማብቃት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ የተጀመሩ የትምህርት ኢንሸቲቮችን ለማሳካት ሁሉም የትምህርት ባለድርሻዎች ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩም የክልል፣የዞንና ወረዳ ትምህርት አመራሮች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርና ሱፐርቫይዘሮች እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation



