የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው።
**********
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018ዓ.ም ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው።
በግምገማ መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ በትምህርት ዘመኑ በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ እቅድ በማቀድና እቅዱን በማስተዋወቅ፣ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ መድረኮች፣ ሀብት የማሰባሰብና የተማሪ ምዝገባ ስራን በንቅናቄ ማስጀመር ስራዎች በስፋት መሰራታቸውን አንስተዋል። በተማሪ ምዝገባም ካለፉት ሁለት አመታት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር አሁን ላይ የተሻለ አፈፃፀም ተመዝግቧል ነው ያሉት። በተለያዩ ችግሮች ደረጃቸው ያልተሻሻሉና በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች ቢኖሩም በየአካባቢው የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል የተሰሩ ስራዎችና የተገነቡ መማሪያ ክፍሎች አበረታች እንደሆኑ ተገልጿል። የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እየተደረገ ያለው ጥረትም የተሻለ እንደሆነ አቶ መኳንንት አደመ ገልፀዋል። የትምህርት ቤት ተማሪዎች ምገባ ኢንሸቲቭ በከተሞችና አንዳንድ ዞኖች በስፋት እየተሰራበት ነው ብለዋል። የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባትና በመደበኛ ትምህርት ቤቶች ራሳቸውን በማስቻል በኩልና የድጋፍና ክትትል ስራዎቻችን ተስፍ ሰጭ ውጤቶችን እያመጡ መሆኑን ም/ቢሮ ኃላፊው አብራርተዋል።
በግምገማ መድረኩ የሰሜን ሸዋ፣ ደብረብርሐን፣ ምስራቅ ጎጃም እና ደብረማርቆስ ከተማ የዞንና ወረዳ ትምህርት አመራሮች፣ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau



