======
ጥር 26/2018 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የተስማሚ ቴክኖሎጅ ማዕከል የድርጅት ባለቤት ዶክተር ታምሩ እውነቱ ዛሬ በአካል ተገኝተው ለአይነስውራን መንቀሳቀሻ አገልግሎት የሚውሉ 300ሽህ ብር የሚያወጣ የመመሪያ ነጭ በትር /ዋይት ኬን/ ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስረክበዋል።
በርክክብ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግስቱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ድጋፍ ላደረገው ድርጅት ምስጋና ያቀረቡት ወ/ሮ እየሩስ
የልዩ ፍላጎት ትምህርት መርሃግርን ውጤታማ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ተመሳሳይ ድጋፎች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።
የድርጅቱ ባለቤት ዶክተር ታምሩ እውነቱ ለአይነስውራን መንቀሳቀሻ አገልግሎት የሚውሉ ዋይት ኬይን ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከዚህ በፊትም ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው በቀጣይም ድርጅቱ ለአይነ ስውራን ተማሪዎች አገልግሉት የሚውሉ ግብአቶችንና ስልጠናዎችን በመስጠት ከቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation



