በሰው ሀብት ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው Human Capital Operation (HCO) ፕሮግራም ከሚተገበርባቸው ወረዳዎች ጋር ምክክር መድረክ ተካሄደ።
ጥር 8/2018 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ Human Capital Operation (HCO) ፕሮግራም ከሚተገበርባቸው ወረዳዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በምክክር መድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አደመ Human Capital Operation (HCO) ፕሮግራም የሚተገበርባቸው ወረዳወች ስለ አሰራሩ ግልጽነት በመፍጠር እና የበለጠ በመረዳት በንቅናቄ መተግበር ይገባል ብለዋል።
ፕሮግራሙ የሰው ልጅ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚተገበር በመሆኑ የተመደበውን ሃብት የፕሮግራሙን ዓላማ መሰረት በማድረግ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በመተግበር እና ለታለመለት ዓላማ ብቻ በማዋል የትምህርት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ፕሮግራሙ የሚተገበርባቸው ወረዳወች እስካሁን ያከናወኗቸውን ተግባራት በተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል።
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የፕሮጀክቱ ፎካል መላኩ አያሌው Human Capital Operation (HCO) ፕሮግራም በአማራ ክልል ሰባት ልዩ ትኩረት በሚሹ ወረዳዎች በአለም ባንክ ድጋፍ የሚተገበር ፕሮግራም መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሮግራሙ በውጤት እና የኢንቨስትመንት ፋይናንሲንግ ሲስተምን መሰረት በማድረግ የሚፈጸም መሆኑ ተመላክቷል።
Human Capital Operation (HCO) ፕሮጀክት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት አልፈው ወደ አንደኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ማሳደግ፣ የሴቶችን ከፍል ወደ ክፍል የማለፍ ምጣኔ ማሳደግ እና ለ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ስለ አካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation



