በምክትል ርዕሰ አሥተዳደር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ.ር)፣የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ካሳሁን አዳነ፣የደብረ ብርሃን ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ መቅደስ ብዙነህ የተመረጡ ትምህር ቤቶችን የሥራ ሂደት ተዟዙረው ተመልክተዋል።
የብሩህ ተስፋ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሥራ ፣የክልል አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የማብቃት ስራ ፣የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የትምህርት አሰጣጥ ሂደት የጉብኝቱ አካል ኾነዋል።
የአንድነት ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ እና የዶሮ እርባታ፣የጓሮ አትክልት ልማት፣የአይሲቲ መማሪያ ክፍል፣ የተማሪዎች የመረጃ አያያዝ ስርአት፣ራይት ቱ ፕለይ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለ10 ትምህርት ቤቶች ያደረገው ድጋፍ፣የሳይንስ መምህራን ስልጠናን ተመልክተዋል።
መረጃው የደብረብርሐን ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *