**
በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ በመምህራኖቻቸው ድጋፍና ክትትል ሴቶች ተሳትፎቸው እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል።
ተማሪ ኑሀሚን ወርቅነህ እና ሰምሪና ሲራጅ በከሚሴ ከተማ የ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው በትምህርት ቤታቸው በመምህራኖች ድጋፍና ክትትል ተሳትፎዎችን እያደገ መጥቷል ብለዋል። ሴቶች ከወንዶች እኩል መድረስ ያለባቸው ትልቅ ቦታ መድረስ እንደሚችሉ ገልፀው የተሻለ ውጤት በማምጣት እራሳቸውንና ትምህርትቤታቸውን ለማስጠራት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
ከትምህርት ጎን ለጎን በክበባት በመደገፋቸው በራስ መተማመናቸውን እንዳሳደገላቸውም ገልፀዋል።
የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ መምህር እና የጀንደር ክበብ ተጠሪ መምህር ዘርፍሽ ታደሰ ሴቶች የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በትርፍ ጊዜ ማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት እና በችግር ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የተሻለ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ እንድሪስ አህመድ እንደገለፁት ሴቶች ላይ ከዚህ በፊት ከነበረው የአመለካከት ችግር በመውጣት ሴቶች በሚገባቸው ቦታ ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከ52% በላይ የሴቶች ተሳትፎ ሲሆን ከዚህ በፊት በሴቶች ላይ የስራ ጫና እና በማህበረሰቡ የነበሩ አመለካከቶችን በመስበር ሴቶችን ወደ ፊት እንዲወጡ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በብሄረሰብ አስተዳደሩ የተሻለ ትውልድን የማነፅ ስራ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በምክትል ደረጃ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን በክልሉ የትምህርት ሽፋን እና የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ሰፊ ስራ መሰራቱን የገለፁት ሀላፊው ባለፋት አመታት የሴቶችን ቁጥር ከወንዶች ለማመጣጠን በተሰራው ስራ በርካታ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል።
በዚህም በክልሉ ከተመዘገቡ 58%ፐርሰንት ተማሪዎች መካከል የሴቶች ተሳትፎ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳልም ነው ያሉት ።
ትምህርት ቤቶች ለሴቶች መማር ማስተማር ሂደት ምቹ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ሀላፊው የሴት ተማሪዎችን ተሳትፎና ውጤታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀው ሴት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በክልሉ ከ13 በላይ ያሉ ክበባቶች ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እየተሰራ ነው ብለዋል።
ሴቶች ውጤታማ እና የተሻለ ቦታ መድረስ እንደሚችሉ ማህበረሰቡ እያየ ሲሆኑ ከዚህ በፊት ማህበረሰቡ ላይ ያለው አመለካከት እየተቀረፈ መምጣት መቻሉንም ገልፀዋል።
በቀጣይ አጠናክሮ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
መረጃው የኦሮሞ ብ/አስ/ኮሙዩኒኬሽን ነው።
ታህሳስ 14/2018

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *