ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም /ትምህርት ቢሮ/ ባለፈው ክረምት ወቅት ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የተዘጋጀው የማሰልጠኛ ሞጁውል እየተገመገመ ነው።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለውጥ ተከትሎ የመምህራን እና የትምህርት አመራሮችን አቅም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ለበርካታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና አመራሮችን ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከ9 ሽህ 7 መቶ በላይ ለሚሆኑ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና አመራሮችን የማሰልጠኛ ሞጁል በማዘጋጀት ባለፈው ክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠና የወሰዱ መምህራን በመማር ማስተማር ሂደታቸው ላይ መነቃቃት መፍጠሩ ተገልጿል።
የማሰልጠኛ ሞጁሉ ግምገማ ከሰልጣኞች እና አሰልጣኝ መምህራን በተሰበሰቡ አስተያየቶች መሰረት ጥንካሬዎች እና ድክመቶችን በመዳሰስ የበለጠ አዳብሮ ለቀጣይ የአቅም ግንባታ ማሰልጠኛ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አቶ ደምስ እንድሪስ ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ እየሩስ መንግስቱ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለውጥን ተከትሎ ለመምህራን ደረጃ በደረጃ የአቅም ግንባታ ስልጠና በቅንጅት መሰጠቱ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation


