የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ የሰሜን ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ የ5 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ባካሄደበት ወቅት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በክልላችን በኮቪድ 19፣ በሰሜን ጦርነት፣ በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነው መቆየታቸውን አውስተዋል።
ኃላፊው ያልተማረ ሕዝብ በመጭው ዘመን ተወዳዳሪ መሆን የማይችል መሆኑን በመረዳት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የልጆቻችን እድሜ በከንቱ እንዳይባክን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ የሁላችንም ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝቦ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ተመዝግበው ትምህርት የጀመሩ ተማሪዎችን ለደረጃው የሚመጥነውን እውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ማስተማር የአእምሮ ስራ በመሆኑ ለመምህራን ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር እና ነጻነታቸውን መጠበቅ እንደሚገባ ኃላፊው አመላክተዋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ መምህራን የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በመፍታት ደስ ብሏቸው ስራቸውን እንዲሰሩ ለማስቻል በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ወላጆች ብሎም ህብረተሰቡ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ገንቢ ለሆኑ መምህራን አክብሮት እንዲሰጥ እና ድጋፍ እንዲያደርግ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *