የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የይሁኔ ወልዱ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ጉብኝት አካሄዱ።
*************
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የይሁኔ ወልዱ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መማር ማስተማሩንና የትምህርት ቤቱን መሠረተ ልማቶች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ የተገኙ ሲሆን በጉብኝታቸውም ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀው መምህራንና የትምህርት አመራሩ ዋና ተልዕኮ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎች እንዲወጡ ማድረግ ላይ መሆን አለበት ብለዋል። አሁን ላይ መምህራን ተማሪዎችን ለማብቃት እያደረጉ ያሉትን ጥረት አመስግነዋል። አያይዘውም ትምህርት ቤቱ ያለበትን የግብዓትም ሆነ ሌሎች ችግሮች በቀጣይ በተጠና ሁኔታ ለመፍታት ቢሮው ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau



