****************
o ከመጽሐፍ ስርጭትና ህትመት ጋር በተያያዘ ለተጠየቁት ጥያቄዎች የመጽሐፍ ህትመት፣ አቅርቦትና ስርጭት ካለፉት አመታት አኳያ ሲታይ ሰፊ መሻሻል የታየበትና ትልቅ ለውጥ የመጣበት እንደሆነ፤ ሆኖም ግን በክዘና ማዕከላት፣ በዞንና ወረዳ የታዩ የስርጭት ችግሮችን በቀጣይነት ለመፍታት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡ ሆኖም ግን የመጽሐፍ አያያዝና አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ያጋጠመንን ሰፊ ችግር የተማሪ ወላጆች ልጆች መጽሐፍትን በጥንቃቄ እንዲይዙ፣ ለቀጣይ ተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጥ መደጋገፍ ይጠይቃል ብለዋል፡፡
o የትምህርት ቤቶች መማሪያ ህንጻ ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ካላቸው ምቹነት ጋር በተያያዘ ለተጠየቁት ጥያቄዎች ነባር የትምህርት ቤቶች ህንጻዎች ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በሚፈለገው ልክ ምቹ አለመሆናቸውን ገልጸው እነሱንም ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አዲስ የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች ከዲዛይን ጀምሮ ልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው ችግር አይስተዋልባቸውም ብለዋል፡፡
o በተለያዩ ጊዜ ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች በተመለከተ መልሶ ለመገንባት ለተለለያዩ ባለድርሻ አካላት ጥሪ ቀርቧል፡፡ ችግሩን በመንግስት አቅም ብቻ መፍታት አይቻልም፡፡ ህዝቡ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት፣ አጥር፣ ሌሎች ግብዓቶችን ማሟላት እንዳለበት ተብራርቷል፡፡ በተለይ በአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎ መሟላት የሚገባቸው የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት መሟላት እንዳለባቸው ተገልጷል፡፡ ለዚህም ማህረሰቡ የአንበሳውን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
o በፌደራል መንግስቱ 11 ትምህርት ቤቶች ለመገንባት እንቅስቃሴ የተደረገ ሲሆን 4ቱ ትምህርት ቤቶች በግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ተብራርቷል፡፡ በክልሉ መልሶ መቋቋም ፈንድ ጽ/ቤት የበጀት ድጋፍ 316 ሚሊየን ብር 63 ትምህርት ቤቶች ለመገንባት ወደ ስራ መገባቱን ቢሮ ሃላፊው አብራርተዋል፡፡ ትምህርት ቤቶችን ለማጠናቀቀም ወረዳዎች ማችንግ ፈንድ መመደብ እንዳለባቸው ነው የተገለፀው፡፡
o የትምህርት ቤቶች ተማሪ ምገባ ስራ በተመለከተ በስፋት ወደ ስራ እንደተገባ ተብራርቷል፡፡
o በአንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ ንቅናቄ በሚሊየን የሚቆጠር የትምህርት ቁሳቁስ መሰብሰቡንና የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች መቅረቡን ያነሱት ሃላፊው በዚህ በጎ ተግባር ለተሳተፉ አካላትም በምክርቤቱ ፊት አመስግነዋል፡፡
o በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መጽሐፍ ትውውቅ ከዚህ በፊት በርካታ መምህራን መሰልጠናቸውን ያብራሩት ሃላፊው በቀጣይም ስልጠና ባልተሠጠባቸው የትምህርት አይነቶች የአሰልጣኞች ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጷል፡፡
o የጎልማሳና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ላይ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ተብራርቷል፡፡
o ተቋርጦ የነበረው መርሱ ዝውውር በ2018ዓ.ም በአዲሱ በተሸሻለው የመምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ዝውውር አፈጻጻም መመሪያ መሰረት እንደሚፈጸም የተከበሩ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ለምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡


