=============
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለዞን እና ወረዳ መምህራን እና ትምህርት ቤት አመራሮች ሙያ ፈቃድ እና እድሳት ባለሙያዎች የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና አስመልክቶ ስልጠና እየሰጠ ነው።
በስልጠና መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ በዚህ አመት ከ27 ሽህ በላይ ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
21 ሽህ 669 ነባር እና 5 ሽህ 559 ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ የሚመረቁ እጩ መምህራን ምዘና ይሰጣል ብለዋል።
የምዘና ሂደቱን ለማቀላጠፍ ለመምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች እና በየደረጃው ለሚገኙ አጋር አካላት ሁሉ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል።
መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት መያዛቸው የበለጠ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችላቸዋል።
በሞዴል እና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር መምህራን ከሚጠየቁት መረጃዎች መካካል የሙያ ፈቃድ ምዘና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ዋነኛው እየሆነ በመምጣቱ ምዘና መካሄዱ የመምህራንን የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈታ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን @amharaeducation bureau
6. ትዊተር :- twitter.com/AmharaEducation

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *