የተማሪዎች ምገባ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገለጸ
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ በ018 ዛሮታ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያለው የተማሪዎች ምገባ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ ያነጋገርናቸው መምህራንና ባለድርሻ አካላት ገልጸዋል።
የጋዝጊብላ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በ018 ዛሮታ ቀበሌ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባን ተመልክተዋል።
ተማሪዎች መመገብ መቻላቸው በህፃናት አዕምሯዊ ዕደገትና ለትምህርት ጥራት አወንታዊ ውጤት እንዲመዘገብ አስችሏል ነው የተባለው።
ውጤታማ እና ሀገር ተረካቢ ትውልድ የሚገነባው ህፃናት ላይ ሲሠራ ነው ያሉት የጋዝጊብላ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ዋና ሀላፊ አቶ አዳነ ሙሉ፦ ይሄን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራት በወረዳው እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራሙ የተጀመረው ለቅድመ መደበኛ ተማሪዎች መሆኑን ያነሱት አቶ አዳነ በትውልድ መሰረት ላይ ጠንክሮ መሥራት የነገዋን የኢትዮጵያን ዕድል የተሻለ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው የምገባ ፕሮግራሙ ለተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ ጤናማና አእምሯቸው የዳባረ ሆነው እንዲያድጉ እንዲሁም በውጤታቸው የተሻለ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል ብለዋል።
የተማሪዎች ምገባ ከተጀመረ ወዲህ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የመምጣት ፍላጎታቸውን እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የ018 ዛሮታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር በላይ ዳረጎት ናቸው።
በሎጎ ኦፍ ፋውንዴሽን ( log of foundation ) ድጋፍ የምገባ ፕሮግራሙ ተግባራዊ ከሆነ ወዲህ በተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታቸው ላይ ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ጠቁመዋል። ይሄንን ውጤታማ ለማድረግም ትምህርት ቤቱ ክትትል እና ቁጥጥር እያደረገ ነው ብለዋል።
የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም የተማሪዎች የማቋረጥ መጠን ከመቀነስ ባሻገር ለትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል።
እየተተገበረ ያለው የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ በማሳደግ፣ የተማሪዎች ቁጥር በየጊዜው እንዲጨምር በማድረግ፣ የትምህርት ውጤትን በማሻሻልና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በማሳደግ በኩል ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የሊጎ ኦፍ ፋውንዴሽን አመቻች መምህርት መልካም ሞላ ተናግራለች።
የጋዝጊብላ ወረዳ Lego Faundation የCDA ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰለሞን ዝናቡ እንደገለፁት፦ ህፃናትን የተሟላ የትምህርት ፓኬጅ በማመቻቸት የመማር ማስተማሩን ሂደትና በድርጅቱ እየቀረቡ ያሉ ሃብቶች ለታለመለት ዓላማ እየዋለ ስለመሆኑ እና በጋራ ተቋማት መሟላት ያለባቸውን ተግባራት ተሟልተው በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን አብራተዋል ።
በሌጎ ፋውንዴሽን የCDA ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ህፃናት ላይ በትምህርት ቤትና በወላጆችም ትምህርቱን እንዲያገኙ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
በዚህ ፕሮጀክት ህፃናትን በምገባ ፕሮግራም ፣ለህፃናት በቤት ውስጥና በቤት ውጭ የመማርያ ቁሳቁስ አሟልተው በመስጠት ከዚህ ውጭ ደግሞ ወላጆችን በተለያዪ ዘርፍ እያሰለጠነ የህፃናት ደህንነትና እድገት ዙርያ ሰፊ ለውጦች እንዲመጡ ድርሻውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
መረጃው የጋዝጊብላ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *